ebook img

Untitled - Amazon AWS PDF

282 Pages·2014·6.62 MB·English
by  
Save to my drive
Quick download
Download
Most books are stored in the elastic cloud where traffic is expensive. For this reason, we have a limit on daily download.

Preview Untitled - Amazon AWS

ዎ ዎ 2 ተስፋ Eንዳትቆርጥ የሚያስፈልግህ ኀይል   ጽ ና ት ጆን ቢቮሬ የሰይጣን ሽንገላ የተሰኘው ከፍተኛ ተነባቢ መጽሐፍ ደራሲ ትርጒም፡- በተስፋዬ መስፍን ተስፋ Eንዳትቆርጥ የሚያስፈልግህ ኃይል - ጽናት በጆን ቢቭሬ John Bevere © 2014 Messenger International www.Messegerinternational.org Originally Published in English ከ www.cloudlibrary.org በነጻ ለመውሰድ በAማርኛ ያሉ ተጨማሪ መጻሕፍት፡- የሰይጣን ሽንገላ - በጆን ቢቭሬ፤ የጽናት መጽሐፍ የጥናት መመሪያና በጽሞና ማሰላሰያ - በጆን ቢቭሬ - Eንስት Aንበሶቹ ይነሣሉ - በሊዛ ቢቭሬ Eንዲሁም የ30 ደቂቃ መልEክቶች የያዙ 12 ቪድዮና Oዲዮ ሲዲዎች፡፡ ለማባዛት፣ በIንተርኔት ለማሰራጨት፣ ጠቃሚ ሐሳቦችን ለመጠቀም ወይም ይህን የAማርኛ መልEክት ከሌሎች ጋር ለመከፋፈል ትበረታታላችሁ፡፡ የመጽሐፉን ደራሲ ለማግኘት - [email protected] Translated to Amharic by – Tesfaye Mesfin Computer Setting by – Betelhem Minas ማውጫ መግቢያ …………………………………………………………….. 1 1. ጽናት - የAንድ ነገር ፍጻሜ ከጅማሬው ይሻላል…………………. 4 2. በሕይወት መንገሥ………………………………………………… 16 3. የኃይሉ ምንጭ …………………………………………………… 29 4. Iየሱስ የተመላለሰው Eንዴት Eንደ ነበር ……………………… 40 5. ራስን መለየት፣ ልቆ መገኘት …………………………………… 52 6. ማየት ወይስ መግባት …………………………………………… 74 7. ከመከራው በስተ ጀርባ ያለው ማነው? ………………………… 94 8. ታጥቃችሁ ተነሡ ……………………………………………… 115 9. በጸጋው በርቱ …………………………………………………… 132 10. የትሕትና መሣሪያ ……………………………………………… 139 11.ሸክምን Eንጣል ………………………………………………… 154 12.ራሳችን ግዙ፤ ንቁ ……………………………………………… 173 13.ዲያቢሎስን ተቃወሙት ………………………………………… 187 14.ላቅ ያለ የመቃወም መንገድ …………………………………… 204 15.ጽናት ያለው ጸሎት …………………………………………… 219 16.ሽልማት Eንደሚቀበል ሩጡ …………………………………… 235 17.ወደ ንጉሡ መቅረብ …………………………………………… 250 18.ተስፋ Aትቁረጡ! ……………………………………………… 258 ተጨማሪ - ሀ የEግዚAብሔር ልጅ ለመሆን ጸሎት …………………………… 268 ተጨማሪ - ለ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች የተጠቀምኩበት ምክንያት… 271 ለማስታወስና ለውይይት …………………………………………… 272 1   መግቢያ ይ ህን መጽሐፍ ማዘጋጀት ከመጀመሬ ጥቂት ቀደም ሲል የጽናትን Aስፈላጊነት በሚገባ የሚያሳይ Aንድ ፊልም ይቼ ነበር፡፡ ፊልሙ በሚካኤል ዳግላስ Eና በቫል ኪልመር መሪ ተዋናይነት የተሠራ The Ghost and the Darkness የተሰኘ ሲሆን ታሪኩ በ1800ዎቹ ማለቂያ የሆነ ጉዳይ ላይ የተመሠረተ ነበር፡፡ በፊልሙ መሠረት ብሪቲሾች የምሥራቅ Aፍሪካን የባቡር መስመር ዝርጋታ ለማፋጠን የዩጋንዳን ሳቮ ወንዝ Aልፎ የሚሄድ የባቡር መስመር ሥራ ግንባታ Eንዲቆጣጠር Aንድ ፓተርሰን (ቫል ኪልመር) የሚሉት ባለ ብሩህ AEምሮ ወታደራዊ መሐንዲስ ተቀጥሮ ነበር፡፡ ፓተርሰን ወደ ቦታው በሄደ ጊዜ Eንኳ ፕሮጀክቱ በጣም ወደ ኃላ ተጓትቶ ነበር፡፡ ምክንያቱን ለማወቅ ጊዜ Aልወሰደበትም፡፡ በየጊዜው ሠራተኞች Eየጠፉ ነበር፡፡ ጨለማን ተገን በማድረግ ድጋሚ Eዚያ ቦታ ላለመገኘት ይሰወሩ ነበር፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ሰዎች Eየበሉ የነበሩ ሁለት Aንበሶች መሆናቸውን ፓተርሰን ወዲያውኑ ተረዳ፡፡ Eነርሱን በመግደል ሰዎች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ለማስቆም ወጥመድ Aደረገ፤ የተለያዩ ዘዴዎችን ሞከረ፤ ሆኖም ሁለቱ Aንበሶች የፓተርሰንን Eንቅስቃሴ Aስቀድመው ያወቁ ይመስል ወጥመዱ Eንዳይዛቸው ጥንቃቄ ያደርጉ ነበር፡፡ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ሰላሣ ሲደርስ የባቡር መሥመሩ ሥራ ኃላፊዎቹ ቻርለስ ሬሚንግተን (ሚካኤል ዳግላስ) የሚባል Aሜሪካዊ Aዳኝ ቀጠሩ፡፡ ይህ ሰው በAደን ሙያው የታወቀ ቢሆንም፣ Aንበሶቹ ግን ማጥቃታቸውን Eንደ ቀጠሉ ነበር፡፡ በየሌሊቱ ሰዎች ይበሉ ነበር፤ በኃላም ሠራተኞቹ፣ ‹‹Eነዚህ Aንበሶች ክፉ መናፍስት ናቸው፤ ማንም ሊያስቆማቸው Aይችልም›› የሚል መደምደሚያ ላይ ደረሱ፡፡ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 130 ሲደርስ የሥራው ካምፕ ሰዎች በጣም ተሸበሩ፤ በጣም ግራ ተጋቡ፤ ፓተርሰንና ሬሚንግተንም ጠቅላላ ሠራተኞች በሳቮ በሚያልፍ ባቡር ላይ Eየተንጠለጠሉ ሲሸሹ ተስፋ ቆርጠው ከማየት በቀር ምንም ማድረግ Aልቻሉም፡፡ Eኔንም ያነሣሣኝ ይህ የሕይወትን ሐቅ የሚያሳይ ሁኔታ ነበር፡፡ መስመሮቹ በግልጽ ተሰምረዋል፡፡ በAንድ በኩል ለመፈጸም የተስማሙትን ሥራ ጥለው Eንዲሄዱ የሠራተኞቹን ፍርሃት Eያባባሰ ያለ ተቆጣጣሪው Aለ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሬሚንግተንን፣ ፓተርሰንን Eና የፓተርሰን ረዳትን 2   የመሳሰሉ ከተግባራቸው ወደ ኃላ የማይሉና ፍርሃት Eጅ Eንዲሰጡ ያላደረጋቸው ሦስት ሰዎች Aሉ፡፡ Aሁን Aደገኞቹን ጠላቶች ለመጋፈጥ ሦስቱ ሰዎች ብቻ ቀርተዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ሊገድሏቸው Eየሞከሩ ሳይሆንላቸው ቀርቷል፡፡ ፊት ለፊታቸው ያለው ግዳጅ Aሰልቺና Eጅግ ሲበዛ Aደገኛ ነበር፡፡ ከዚያም በላይ ሕይወታቸውን Eንኳ ሊያሳጣቸው ይችላል፤ ያም ሆኖ ግን ችግሩን ለማስቆምና ድልድዩን ለማስጨረስ ቆርጠዋል፡፡ በዘመኑ Aሉ የተባሉ መሣሪያዎች ይዘዋል፡፡ በጥበብ፣ በንቃት፣ በቆራጥነት ከተንቀሳቀሱ Eና ተስፋ ካልቆረጡ መጨረሻ ላይ Eንደሚያሸንፉ ሬሚንግተንና ፓተርሰን Eርግጠኞች ነበሩ፡፡ Eዚህ ላይ ብዙ ዝርዝር ነገር ለማቅረብ ቦታውም ጊዜውም Aይበቃም፣ ግን ይህን በሚገባ ማወቅ Aለባችሁ - በመጨረሻ ሰው በላ Aንበሶቹ ጥቃታቸውን ያቆማሉ፡፡ ሆኖም፣ ያ ድል የሚገኘው ትልቅ ዋጋ ተከፍሎ ነው፡፡ Aሁን ችግሩ መፍትሔ ስላገኘ ሠራተኞቹ ወደ ሥራ ቦታቸው መመለስ ጀመሩ፣ Aሁን የፕሮጀክቱ መሐንዲስ ፓተርሰንን የሚያዩት በጣም በተለየ ሁኔታ ሆኗል፡፡ ሞትን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ለሁኔታው Aስቸጋሪነት Eጅ ያልሰጠ Eርሱ ነበር፡፡ ሰዎቹ ለEርሱ Eጅግ ከፍ ያለ ከበሬታ ስለ ነበራቸው የማይቻል የሚመስል ነገር Eንኳ ለመፈጸም ከኃላው ለመሰለፍ ፈቃደኞች ሆነዋል፡፡ የድልድዩም ሥራ በተወሰነለት ጊዜ ተጠናቀቀ! Eንደ የEግዚAብሔር Eንደራሴዎች (Aምባሳደሮች) Eኛም ድልድይ Eየሠራን ነው፡፡ የEኛ ድልድይ ወንዞች የሚያሻግር ሳይሆን፣ በሰማይና በምድር መካከል የተዘረጋ ነው፡፡ Eኛም Eንዲሁ ተቃውሞ Aለብን፤ መጽሐፍ ቅዱስ ጠላታችንን—የሚያገኘውን ሁሉ መዋጥ Eንደሚፈልግ Aንበሳ ብሎታል፡፡ ሆኖም Eንደ Eነዚያ Aንበሶች ሁሉ ጠላታችን መሣሪያ የለውም… Eኛ ግን Aለን፡፡ Eርሱ ትጥቅ Eንዲፈታ ተደርጓል፤ Eኛ ግን የሰው ልጅ ሊኖረው ከሚችለው ሁሉ የበለጠ ብርቱ መሣሪያ Aለን፡፡ ማሸነፍ ያለብን ጦርነቶች Aሉ፤ መቆጣጠር ያለብን ምሽጎች Aሉ፡፡ ብዙ ጊዜ Eነዚህ ነገሮች የAEምሮ ዝንባሌዎችን፣ የAሠራር መንገዶችን፣ ሥረ መሠረት ያደረጉና ጠላት በዚህ ዓለም ሰዎች Aስተሳሰብ ውስጥ የነዛቸው Aመለካከቶች ናቸው፡፡ የሚገጥመን ተቃውሞ Eጅግ ከባድ ነው፤ ይሁን Eንጂ፣ ‹‹በክርስቶስ›› Eኛ ከዚያ ሁሉ በላይ ብርቱዎች ነን፡፡ 3   ስለዚህ ፊት ለፊታችን በጣም Aስፈላጊ ጥያቄ ተቀምጧል - ሕይወታቸውን ለማዳን ከዚያ Aስቸጋሪ ሁኔታ Eንደ ሸሹ ሠራተኞች ነን ወይስ የተሰጠንን ሰማያዊ ኃላፊነት በጽናት የምንፈጽም? በዚህ Aሁን በማቀርበው መልEክት ውስጥ በሕይወታችሁ ጽናት Eንዲጐለብት የሚያደርጉ Eውነቶች Eንዳሉ Aምናለሁ፡፡ Eነዚህ Eውነቶች Eንድትጎብዙና Eንድትበረቱ ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ለማሸነፍና ቀና ለውጥ ለማምጣት በሚያስችላችሁም ኃይል ያስታጥቋችኃል፡፡ በዚህ ውቀት መመሥረታችሁ Eጅግ Aስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ባለ ማወቅ የEግዚAብሔር ሕዝብ ረጅም ዘመን ምርኮ ውስጥ ኖረዋል፤ ይህን በማጣትም ጠፍተዋል (Iሳይያስ 5፥13፤ ሆሴ 4፥6 ይመ)፡፡ ትክክለኛ ውቀት የEምነት መሠረትን ይገነባል፤ Eምነት ደግሞ በጠፋውና በጨለመው ዓለም ውስጥ ለውጥ ማምጣት ያስችለናል፡፡ የተፈጠራችሁት በዙሪያችሁ ባለው ዓለም ቀና ለውጥ Eንድታመጡ ነው፡፡ ተስፋ Eንዳንቆርጥ የሚረዳንን የጽናት ኃይል ለማወቅ በምናደርገው ጥረት በጸሎት መንፈስ ተግዳሮቱን Eንቀበል! 4   1 ጽናት የአንድ ነገር ፍጻሜ ከጅማሬው ይሻላል፡፡ መክብብ 7፥8 Aንድን ነገር፣ ‹‹የምንፈጽምበት›› ሁኔታ፣ ‹‹ከምንጀምርበት›› ሁኔታ የበለጠ ጠቃሚ ነው በሚለው Eሳቤ ከEኔ ጋር Eንደምንስማማ ቁጠሩ፡፡ በክርስትና ሕይወት መሠረት Eንደሚገባ መጨረስ ማለት ጌታ፣ ‹‹Aንተ ታማኝ Aገልጋይ፣ መልካም Aድርገሃል!›› ሲለን መስማት ማለት ነው፡፡ ለEኛ ሁሉም ነገራችን ከሆነው ጌታ Eንዲህ ያሉትን ድንቅ ቃላት ለመስማት Eኔና Eናንተ የሚያስፈልገን ምን ይሆን? ሕይወትን Eንደሚገባ መጨረስ፣ ሕይወትን Eንደሚገባ መኖርን ይጠይቃል፡፡ ይህ ደግሞ፣ ‹‹ተስፋ Aለመቁረጥን›› ማሳደግን የሚጠይቅ መሆኑ Aያጠራጥርም፡፡ በAጭሩ፣ ባለ ጽኑ መንፈስ መሆን ማለት ነው፡፡ ታዲያ ያንን የምናገኘው Eንዴት ነው? ይህን ያህል Aስፈላጊ የሆነውስ ለምንድነው? Eውነቱን ለመናገር ብዙ Aማኞች Eንደሚገባ መፈጸም Aለመቻላቸው በጣም ያሳስበኛል፡፡ Aንድ ጊዜ EግዚAብሔር ከዚህ መጽሐፍ ቢይ ሐሳብ ጋር የሚያያዝ ራEይ ሰጥቶኝ ነበር፡፡1 1. ይህን ራEይ ከዚህ ቀደም በጻፍኩት A Heart Ablazeበሚለው መጽሐፍ በAጭሩ Aንስቼው ነበር፡፡ Aሁን ግን ይህን ታሪክ Eንደ ገና ማቅረብና የበለጠ ማብራራት Eንዳለብኝ ተሰምቶኛል፡፡ 5 ጽናት   Eጅግ Aደገኛ ማበል ባለበት ወንዝ ውስጥ Aንድ ሰው ጀልባ Eየቀዘፈ ነበር፡፡ ከዚያ ማበልና ወጀብ ለመውጣት የሚችለውን ያህል Eየታገለ ነበር - ሥራው Aስቸጋሪ ቢሆንም ከቅም በላይ ግን Aልነበረም፡፡ Eየተዝናኑ ያሉ ሰዎች የያዙ ሌሎች ትልልቅና ምቾት ያላቸው ጀልባዎች በየጊዜው በAጠገቡ ያልፉ ነበር፤ በውሃው ኃይል Eየተነዱ ቁልቁል ይወርዱ ነበር፡፡ በEነዚህ ጀልባዎች የነበሩ ሰዎች ይስቁ ነበር፣ ይጠጡና ዘና ብለው ርፈው ነበር፡፡ Aልፎ Aልፎም ከማበሉ ጋር የሚታገለውን ሰው የት Eያደረጉ ያፌዙበት ነበር፡፡ ወደ ፊት Aንድ ርምጃ ለመሄድ Eርሱ Eያንዳንዷን ስንዝር ይታገላል፤ Eነርሱ ግን ምንም የሚያደርጉት Aልነበረም፤ ቢያደርጉ Eንኳ Eጅግ ሲበዛ ጥቂት ነበር፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኃላ ሰውየው ከማበሉ ጋር በሚያደርገው ትግል ሰለቸ፡፡ በጣም ተዳክሞና ተስፋ ቆርጦ መቅዘፊያዎቹን Aስቀመጠ፡፡ በውሃው ግፊት ወዲያ ወዲህ Eየተላጋ ጥቂት ወደ ፊት ሄደ፤ በኃላ ግን ቀጥ ብሎ ቆመ፡፡ ከዚያም በጣም Aሳዛኝና Aስጨናቂ ነገር ሆነ፣ ጀልባዋ ፊቷን ያቀናችው ወደ ፊት ቢሆንም፣ በወጀብና ማበሉ ተገፍታ ቁልቁል ወረደች፡፡ ሰውየው ወዲያውኑ ሰዎች የሞሉባት Aንድ ጀልባ ያያል፡፡ ይህኛው Eስካሁን ካያቸው ጀልባዎች የተለየ ነበር፤ ልክ Eንደ የEርሱ ጀልባ ሁሉ ፊቱን ወደ ላይ ያቀና ቢሆንም፣ በማበሉ ተገፍቶ ቁልቁል Eየወረደ ነበር፡፡ ይኸኛውም ጀልባ የሚስቁ፣ የሚንጫጩና ዘና ያሉ ሰዎች ይዞ ነበር፡፡ ሰውየው መሄድ ፈልጐ ወደ ነበረበት Aቅጣጫ ወደ ላይ ያቀና ቢሆንም፣ Eንጣጥ ብሎ በመዝለል ወደ Eነርሱ ሄዶ ሊቀላቀላቸው ፈለገ፡፡ በዚህ ጊዜ ሁለቱ ጀልባዎች በጣም ተቀራርበውና ተጠጋግተው ነበር፡፡ ፊታቸውን ወደ ታች ካቀኑትና ወደዚያም Eየሄዱ ከነበሩት ከሌሎቹ ጀልባዎች በተለየ መልኩ ይኸኛው ጀልባ ፊቱን ወደ ላይ Aቅንቶ ነበር፡፡ ይሁን Eንጂ፣ በማበሉ Eየተገፋ በሚያሳዝን ሁኔታ ቁልቁል Eየወረደ ነበር፡፡ የዚህ ራEይ ትርጉም ምንድነው? ወንዙ ይህን ዓለም ይወክላል፤ ጀልባው በዚህ ዓለም ለመኖርና ለመንቀሳቀስ የሚያስችለን የሰው ልጅ Aካል ነው፡፡ ጀልባው ውስጥ የነበረው ሰው Aማኝ ነው፤ መቅዘፊያው Eንዲሁ በነጻ ከEግዚAብሔር የተቀበልነው ጸጋ ምሳሌ ነው፡፡ ሰዎች የነበሩባቸው ጀልባዎች ለAንድ ዓላማ መሰለፍን ያመለክታል፤ ወንዙ ላይ የተነሣው ማበል በክፉው ቁጥጥር ሥር ያለውን የዚህን ዓለም Aካሄድ ይወክላል፡፡ በጸጋ መቅዘፊያ Aማካይነት ሰውየው የEግዚAብሔርን መንግሥት Eያስፋፋ ማበሉን ተቋቁሞ ወደ መጨረሻ ግቡ መድረስ ይችል ነበር፡፡

Description:
በለጠ፡፡ ጀልባ ባልነበረው ጊዜ፣ ባሕሩን መሻገር ፈልጐ ነበር፤ ስለዚህ ውሃው. ላይ ተራመደ፡፡ በሰርግ ቤት ወይን ጠጅ ባለቀባቸው ጊዜ፣ ውሃውን ወደ. ወይን ጠጅ
See more

The list of books you might like

Most books are stored in the elastic cloud where traffic is expensive. For this reason, we have a limit on daily download.